አንድነት 14ኛ ዓመት ቁ. 22 ዓርብ ታህሳስ 23 ቀን 2002 ዓ.ም
በሰሜን ጐንደር የዞንና የወረዳዎችን የማጠናከርና የማስፋፋት ሰፊ ሥራ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ፡፡ በቀጣናው ውስጥ አደራጅና የፓርቲው የመኢአድ ሥራ አስፈጻሚ አባል የሆኑት አቶ ተስፋዬ ታሪኩ እንደተናገሩት የሰሜን ጐንደር ሕዝብ ለለውጥ የተዘጋጀ መሆኑን ለፓርቲው ሥራ በዞኑ ሲንቀሳቀስ የተመለከቱ መሆናቸውን ጠቅሰው በዚህም አራት የወረዳ ጽ/ቤቶችን በሕዝብ ጥያቄ ለመክፈት መቻሉን አስረድተዋል፡፡ በሰሜን ጐንደር ዞን በሕዝብ መዋጮ የተከፈቱት ወረዳዎች አርባያ፣ በለሳ /ጉሐላ/፣ ገደቡጌና ማክሰኝት ላይ ሲሆን ሌሎች ተጨማሪ ጽ/ቤቶችን ለመክፈት ዝግጅት ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡ በሌላም በኩል በደቡብ ጐንደር ቦልጋ እና ቆላድባ ወረዳዎች ላይ ጽ/ቤት የተከፈቱ ሲሆን በቅርቡ ሥራ እንደሚጀምሩም ገልፀዋል፡፡
አንድነት ድርጅት /መኢአድ/ በትግራይ ክልል አራት ተጨማሪ ጽ/ቤቶችን የከፈተ መሆኑን የመኢአድ የማእከላዊ ኮሚቴ አባልና በትግራይ አደራጅ የሆኑት ወ/ሮ መሰሉ ረዳ ገለፁ፡፡ የተከፈቱት ጽ/ቤቶች ሶስት የዞንና አንድ የወረዳ ሲሆኑ በአጋሜ ዞን አዲግራት፣ አክሱም፣ ሽሬ እንደስላሴ እና በኮረም የወረዳ ጽ/ቤቶች ናቸው፡፡ የነዚህ ተጨማሪ ጽ/ቤቶች መከፈት በትግራይ ክልል የሚደረገውን የፓርቲውን እንቅስቃሴ እንደሚያሰፋ ወ/ሮ መሰሉ አስረድተዋል፡፡ ተጨማሪ ጽ/ቤቶች የተከፈቱባቸው አካባቢዎች በክልሉ ውስጥ ከሚገኙ ዞኖች ውስጥ ብዛት ያለው የምርጫ ጣቢያዎች ላላቸው ዞኖች ቅድሚያ የተሰጠ መሆኑን የገለፁት ወ/ሮ መሰሉ በቀጣይም ተጨማሪ የዞን ጽ/ቤቶችን ለመክፈት በዝግጅት ላይ መሆናቸውን አሳውቀዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በትግራይ ስድስት የመኢአድ ጽ/ቤቶች ተከፍተው የፓርቲውን ሥራ በማከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡::
ለማንበብ ከዚህ ላይ ይጫኑ