About Us
  • About Kinijit AEUP
  • Political Program
  • Election 2005
  • Election 2010
  • USA
  • Canada
  • Europe
  •   News
  • Amharic
  • English
  • Washington Update
  •   Editorial & Opinions
  • Editorial
  • Opinion
  •   Media
  • Audio
  • Video
  •   Press Release
  • English
  • Amharic
  •   Burning Issues
  • Economy
  • Education
  • Health
  • HR2003 to S3457
  • Regional Crisis
  • Politics & Democracy
  • Others
  •   Facts about Ethiopia
  • All Ethiopia Gallery
  •   Take Action
  • Make a Contribution
  • Join our Supporters
  •    Subscribe to Andenet
         Gazette
      Calendar
  • Calendar
  •  
     
      Home Contact Us   Font help

    መኢአድ የምርጫ ሕጉ እንዲሻሻል ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ደብዳቤ ጻፈ


    የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት /መኢአድ/ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በአዋጅ ቁጥር 532/1999 ዓ.ም የፀደቀውን የምርጫ ሕግ መሰረት በማድረግ በደንብና መመሪያዎቹ ላይ የተደረገውን የማሻሻያ ሐሳብ አስመልክቶ ለፓርቲው በላከው ሰነድ ላይ ያለውን አቋም ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በደብዳቤ አሳወቀ፡፡    

     
    የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በመጋቢት ወር 2ዐዐ1 ዓ.ም ለሁሉም ፓርቲዎች በላከው ሰነድ በአዋጁ መሰረት አራት ደንቦችና ስድስት መመሪያዎች ያሉት የማሻሻያ ሐሳብ ሲሆን እያንዳንዱ ፓርቲ በመመሪያውና በደንቡ ላይ ያለውን ቅሬታ እንዲገልጽና መሻሻል የሚገባቸውን ነጥቦች በጽሑፍ ለቦርዱ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ እንዲያስገባ የሚያሳስብ ነው፡፡  
     
    መኢአድ ከምርጫ ቦርድ የተላከውን ሰነድ የሚያጠና ኮሚቴ አቋቁሞ በአዋጁ፣ በደንቦቹንና በመመሪያዎቹ ላይ ሰፊ ጥናት አድርጓል፡፡ በመሆኑም ከመመሪያውና ከደንቡ ይልቅ መሰረታዊ ማሻሻያ መደረግ ያለበት በአዋጁ ላይ መሆኑን አጥብቆ እየገለፀ ይገኛል፡፡  
     
    መኢአድ በጻፈዉ ደብዳቤ ላይ ገዢው ፓርቲ ለራሱ እንደሚመቸው አድርጐ ያስቀመጣቸውን አንቀጾች አገርና ሕዝብን በሚጠቅም መልኩ መሻሻል እንዳለባቸውና አሁን ባለው ሁኔታ ግን ሕጉ አሳሪ ሆኖ እያለ ተሻሽሏል ማለት እንደማይቻል ጠቅሷል፡፡ ይህም በመሆኑ መኢአድ ከምርጫ ቦርድ መመሪያና ደንብ መሻሻል በፊት መንግስት በ1999 ዓ.ም በፓርላማ ያፀደቀውን አዋጅ 532/1999 /ተሻሽሎ የወጣው የምርጫ ሕግ/ በድጋሚ መሻሻል አለበት ብሏል፡፡  
     
    መኢአድ ከ41 አንቀጾች በላይ መስተካከል አለባቸው በማለት አንቀጾችን በዝርዝር ያስቀመጠ ሲሆን አንቀጾቹ ሊስተካከሉ የሚችሉበትን አማራጭ ሐሳብ የያዘ ሰነድ አቅርቧል፡፡
     
    የምርጫ አዋጅ ቁጥር 532/1999 ማሻሻያ እንደተደረገበት በምርጫ ቦርድ ቢገለጽም በአዋጁ ውስጥ ያሉ ብዙ አንቀጾች መሻሻል እንዳለባቸው መኢአድ ያስገነዝባል፡፡ ዋናው አዋጅ ገንቢ በሆነ መንገድ እስካልተሻሻለ ድረስ ደንቦቹና መመሪያዎቹ የተፈለገውን ውጤት ሊያመጡ እንደማይችሉ ይገልጻል፡፡ ለዚህም ገዢው ፓርቲና ተቃዋሚ ፓርቲዎች በጋራ በመወያየት አዋጁ እንዲዳብር ማድረግ አስፈላጊ ነው ሲል መኢአድ ሐሳቡን አቅርቧል፡፡ የአዋጁ መሻሻል በ2ዐዐ2 ዓ.ም ለሚካሄደው አገራዊ ምርጫ ነጻ፣ ፍትሃዊና ሰላማዊ መሆን ወሳኝ ነው በማለት ገልጿል፡፡
     
    መኢአድ ይህን አቋሙን የሚገልጽ ሁለት ገጽ ደብዳቤና ስምንት ገጽ የማሻሻያ ሐሳብ ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የጻፈ ሲሆን ለምርጫ ቦርድና ለሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎችም መላኩ ታውቋል፡፡

    Comments



       Type in your comments for this article
    Name (appears on your post)
    Email
    Comment

    Write the characters in the image above

    Search News:
    In all newsIn News Amharic

    Advanced Search
    Archive:
    Published in:
    Published between
    and
    Categories:
    all categories
    one or more of the following categories (select as many as you want)
    History
    World News
    Opinion
    Editorial
    News English
    Washington Update
    News Amharic
    Media Audio
    Media Video
    Kinijit AEUP Radio
    Africa News


    Most Viewed News Amharic
    መኢአድ በባሕርዳር ከተማ ታለቅ ስብሰባ አካሄደ - የመጀመሪያዉን የምርጫ ደወል አሰማ
    መኢአድ “ሊበራል ኦፕን-ኤየር ኮሌጅ” መክፈቱን አስታወቀ
    መንግስት ጐንደር ውስጥ ከ6ዐ በላይ ሰዎችን ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ ለአርባ ቀን ያሕል አስሮ መልቀቁ ተገለፀ፡፡
    የጐፋ ልዩ ዞን የገዢው ፓርቲ የጽ/ቤቶቹን ባንዲራ እያወረደበት መሆኑን መኢአድ ገለፀ
    የመኢአድ የደጀን ወረዳ ልዩ ዞን የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት አካሄድ
    የመኢአድ የአርባ ምንጭ ዞን ሰብሳቢና ፀሐፊ ያለ ሕግ አግባብ ታሰሩ
    በምስራቅ ጐጃም አንድ ተማሪ በታጣቂዎች ተገደለ
    Call for a Meeting - ወሳኝ ሰዓት
    መኢአድ በክልል ለሚገኙ የዞን የሥራ ኃላፊዎች ስምምነት በተደረሰበት ሰነድ ላይ ማብራሪያ ሰጠ
    መኢአድ በሰሜን ጐንደርና በትግራይ ተጨማሪ ጽ/ቤቶችን ከፈተ