About Us
  • About Kinijit AEUP
  • Political Program
  • Election 2005
  • Election 2010
  • USA
  • Canada
  • Europe
  •   News
  • Amharic
  • English
  • Washington Update
  •   Editorial & Opinions
  • Editorial
  • Opinion
  •   Media
  • Audio
  • Video
  •   Press Release
  • English
  • Amharic
  •   Burning Issues
  • Economy
  • Education
  • Health
  • HR2003 to S3457
  • Regional Crisis
  • Politics & Democracy
  • Others
  •   Facts about Ethiopia
  • All Ethiopia Gallery
  •   Take Action
  • Make a Contribution
  • Join our Supporters
  •    Subscribe to Andenet
         Gazette
      Calendar
  • Calendar
  •  
     
      Home Contact Us   Font help

    የጐፋ ልዩ ዞን የገዢው ፓርቲ የጽ/ቤቶቹን ባንዲራ እያወረደበት መሆኑን መኢአድ ገለፀ


     

    የጐፋ ልዩ ዞን የገዢው ፓርቲ የጽ/ቤቶቹን ባንዲራ እያወረደበት መሆኑን መኢአድ ገለፀ
     
          በጐፋ ልዩ ዞን መኢአድ ጽ/ቤትና ባስኬቶ ልዩ ወረዳ መኢአድ ጽ/ቤት በተለያዩ ጊዜያት የመንግስት ፖሊሶችና ባለስልጣናት ታፔላዎችንና ሰንደቅ ዓላማዎችን በማውረድ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት እየፈፀሙብን ነው ሲሉ የመኢአድ የጐፋ ልዩ ዞን ኮሚቴ ሰብሳቢና የፓርቲው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ እንድርያስ ኢሮ ለአንድነት ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ገልፀዋል፡፡
     
          አቶ እንድርያስ ኤሮ “በፓርቲው ላይ እየተፈጠረ ያለውን ችግር ለመጠቆም ብንሞክርም የጐፋ ልዩ ዞን የሚለውን አወቃቀርና ታፔላ አንቀበልም ያሉን ሲሆን በምርጫ ቦርድ አዋጅ ቁጥር 46/85 መሰረት ማንኛውንም እውቅና ያለው ፓርቲ የራሱን ጽ/ቤት የመክፈት መብት አለው ብንላቸውም መንግስት ሳያፀድቅ ይህንን ማድረግ አትችሉም የሚል መልስ ነበር የሰጡን፡፡ እኛ ግን የፓርቲያችን ላእላይ ምክር ቤት ወስኖ ፕሬዝዳንታችን ካፀደቁት መክፈት እንችላለን በማለት ብንሟገታቸውም በስተመጨረሻ ይህ ጉዳይ የሚመለከተው ፍርድ ቤቱን ነው በማለት እንዳንሰራ አውከውናል፡፡” ብለዋል፡፡
     
          የገዢው ፓርቲ ታዛዦች ከፍርድ ቤት ትእዛዝ ውጭ በአቃቤ ሕግ ብሩክ አባተ በመመራት የዞኑን የመኢአድ ሶስት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት አስረው እንደነበርም ተገልጿል፡፡ አቶ እንድርያስ ኢሮን የካቲት 5 ቀን ረፋዱ ላይ በመያዝ ለአንድ ቀን ያህል አስረው በዋስ ሲፈቷቸው፣ የዞኑ ፀሐፊ አቶ አበበ ኢልዳድን እና አቶ ሐብታሙ ዱባኤን ከየካቲት 5 ቀን እስከ የካቲት 12 ቀን ድረስ ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ ካሰሯቸው በኋላ በሰባተኛው ቀነ ጉዳዩን ለከፍተኛው ፍርድ ቤት በማቅረብ በዋስ ተለቀዋል ያሉት አቶ እንድርያስ ሌሎቹንም አባሎቻችንን በዚህ መሰሉ ሕገ ወይ ተግባር እያንገላቷቸው ነው ብለዋል፡፡
     
          የካቲት 24 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ከቀኑ 11፡1ዐ ላይ የመኢአድ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን በማሰር የሚታወቁት አቃቤ ሕጉ አቶ ብሩክ አባተ ወደ መኢአድ ጽ/ቤት በመምጣት ታፔላውን በመንቀልና ሰንደቅ ዓአላማውን በማውረድ በመኪና ጭነው መሄዳቸው ታውቋል፡፡ በማግስቱም የመኢአድ የዞኑ የ12 ወረዳ ሰብሳቢዎች በአንድ ላይ ሆነው ጐፋ አካባቢ ፍትሕ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በመሄድ ንብረታች መሰረቁን ጠቅሰው፣ የጽ/ቤቱን ዘበኛ በማስፈራራት ንብረቱን የዘረፋት ግለሰብ ለፍርድ ሊቀርቡልን ይገባል ብለው ቢከሱም ሶስት ጊዜ በቀጠሮ ካመላለሷቸው በኋላ በመጋቢት 8 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም የፍትሕ ማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ እናንተ ክስ ላይ ስላላችሁ እንደገና ሌላ ክስ /ፋይል/ አንከፍትም የሚል መልስ  እንደሰጧቸው ከስፍራው ከደረሰን መረጃ ለማወቅ ተችሏል፡፡

    Comments



       Type in your comments for this article
    Name (appears on your post)
    Email
    Comment

    Write the characters in the image above

    Search News:
    In all newsIn News Amharic

    Advanced Search
    Archive:
    Published in:
    Published between
    and
    Categories:
    all categories
    one or more of the following categories (select as many as you want)
    History
    World News
    Opinion
    Editorial
    News English
    Washington Update
    News Amharic
    Media Audio
    Media Video
    Kinijit AEUP Radio
    Africa News


    Most Viewed News Amharic
    በምስራቅ ጐጃም አንድ ተማሪ በታጣቂዎች ተገደለ
    በሰሜን ሸዋ ዞን ገዥውን ፓርቲ በመቃወማቸው ለስደት መዳረጋቸውን ገለፁ
    68ኛው የድልና የነጻነት በዓል ተከበረ
    መኢአድ በባሕርዳር ከተማ ታለቅ ስብሰባ አካሄደ - የመጀመሪያዉን የምርጫ ደወል አሰማ
    በሰሜን ጐንደር የእስረኞች አያያዝ አሳሳቢ መሆኑ ተገለፀ
    መኢአድ “ሊበራል ኦፕን-ኤየር ኮሌጅ” መክፈቱን አስታወቀ
    መንግስት ጐንደር ውስጥ ከ6ዐ በላይ ሰዎችን ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ ለአርባ ቀን ያሕል አስሮ መልቀቁ ተገለፀ፡፡
    የጐፋ ልዩ ዞን የገዢው ፓርቲ የጽ/ቤቶቹን ባንዲራ እያወረደበት መሆኑን መኢአድ ገለፀ
    የመኢአድ የደጀን ወረዳ ልዩ ዞን የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት አካሄድ
    የመኢአድ የአርባ ምንጭ ዞን ሰብሳቢና ፀሐፊ ያለ ሕግ አግባብ ታሰሩ