About Us
  • About Kinijit AEUP
  • Political Program
  • Election 2005
  • Election 2010
  • USA
  • Canada
  • Europe
  •   News
  • Amharic
  • English
  • Washington Update
  •   Editorial & Opinions
  • Editorial
  • Opinion
  •   Media
  • Audio
  • Video
  •   Press Release
  • English
  • Amharic
  •   Burning Issues
  • Economy
  • Education
  • Health
  • HR2003 to S3457
  • Regional Crisis
  • Politics & Democracy
  • Others
  •   Facts about Ethiopia
  • All Ethiopia Gallery
  •   Take Action
  • Make a Contribution
  • Join our Supporters
  •    Subscribe to Andenet
         Gazette
      Calendar
  • Calendar
  •  
     
      Home Contact Us   Font help

    የመኢአድ የደጀን ወረዳ ልዩ ዞን የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት አካሄድ


     

    የመኢአድ የደጀን ወረዳ ልዩ ዞን የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት አካሄድ
     
    በምስራቅ  ጐጃም ዞን የደጀን ልዩ ወረዳ የመኢአድ አባላት ለሴቶችና ወጣቶች ምክር ቤት ማጠናከሪያ የሚሆን የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ያካሄደ መሆኑ ተገለፀ፡፡
     
          የካቲት 28 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በደጀን ከተማ ከቀኑ 4 ሰአት እስከ 7 ሰዓት ተኩል ድረስ በቆየዉ ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ በርካታ የአመራር ሐላፊዎችና አባላት ተሳታፊ እንደነበሩ ታውቋል፡፡ ከመኢአድ ዋና ጽ/ቤት ተወክለው የክብር እንግዳ የሆኑት የመኢአድ ምክትል ፕሬዝዳንትና የምዕራብ ቀጠና ኃላፊ አቶ አሰፋ ኃብተወልድ እና የሰሜን ቀጠና አደራጅ መቶ አለቃ ወንድም ደፋር በዝግጅቱ ላይ ተገኝተው ስለ አደረጃጀትና ስለወቅቱ ተጨባጭ ሁኔታ እንዲሁም መኢአድ እያከናወነ ስላለው የማደራጀት ሂደት በሠፊው ገልጸዋል ፡፡
     
           በገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቱ ላይ ቲሸርትና መጽሐፍ የሚያስገኙ እጣዎች ተዘጋጅተው የቀረቡ ሲሆን የምግብና የመጠጥ ሽያጭም የገቢ ማሰባሰቢያው አንድ አካል የነበረ መሆኑ ታውቋል፡፡
     
    በዝግጅቱ ላይ ከሶስት መቶ በላይ ተሳታፊ አባላትና ደጋፊዎች እንደተገኙና ሥነ ሥርአቱም እጅግ ያማረ እንደነበር ወደፊትም ሊበረታታ እንደሚገባውና ለሌሎችም ወረዳዎች አርአያ እንደሚሆን ከመኢአድ ዋና ጽ/ቤት ተጋብዘው የተገኙት አቶ አሰፋ ኃብተወልድ ገልፀዋል፡፡
     
    ለሴቶችና ለወጣቶች ምክር ቤት ማደራጃ እንዲሆን ታስቦ በተዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ በቂ ገንዘብ የተገኘ መሆኑም ከስፍራው ከተገኘው ማስረጃ ለማወቅ ተችሏል፡፡
       
    በገቢ ማባሰቢያው ላይ አቶ አሰፋ ኃብተወልድ የመኢአድን አገር አቀፋዊ እንቅስቃሴን አስመልክተው ንግግር ያደረጉ ሲሆን አደረጃጀትና ድርጅታዊ ጉዳይን በሚመለከት ደግሞ መቶ አለቃ ወንድም ለተሳታፊዎች ገለጻ አድርገዋል፡፡
     
          የምስራቅ ጐጃም ዞን አደራጅ አቶ ተስፋዬ ታሪኩ፣ የምስራቅ ጐጃም ዞን ስራ አስፈጻሚና ሰብሳቢ መቶ አለቃ ዮሐንስ አባተ፣ የደጀን ወረዳ የሴቶችና የወጣቶች ጉዳይ ሐላፊዎች የመኢአድ የወረዳ ድርጅታዊ አሰራርን በተመለከተ ሰፊ ገለጻ አቅርበዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከሰባት ወረዳዎች የመጡ የወረዳ ሰብሳቢዎችም የየወረዳቸውን እንቅስቃሴ በተመለከተ ሪፓርታቸውን አሰምተዋል፡፡
     
    በዝግጅቱ ፍጻሜ ላይ የእስልምናና የክርስትና ሐይማኖት አባቶች በየተራ የመዝጊያ ንግግርና ሐይማኖታዊ ምርቃት ሰጥተዋል፡፡ መኢአድም እንዲጠናከር ሠፊ ምክር ለግሰው ስብሰባው ተጠናቋል፡፡ 

    Comments



       Type in your comments for this article
    Name (appears on your post)
    Email
    Comment

    Write the characters in the image above

    Search News:
    In all newsIn News Amharic

    Advanced Search
    Archive:
    Published in:
    Published between
    and
    Categories:
    all categories
    one or more of the following categories (select as many as you want)
    History
    World News
    Opinion
    Editorial
    News English
    Washington Update
    News Amharic
    Media Audio
    Media Video
    Kinijit AEUP Radio
    Africa News


    Most Viewed News Amharic
    የመኢአድ የኪነት ቡድን ሞረሽ በበዓሉ ላይ ጣዕመ ዜማዎች በማቅረብ ላይ ይገኛል፡፡
    የመኢአድ የአ.አ ወጣቶች በበዓሉ ላይ ንግግር አደረጉ፡፡
    በምስራቅ ጐጃም አንድ ተማሪ በታጣቂዎች ተገደለ
    የመሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ተረፈ ምርት በነዋሪዎች ላይ የጤና ችግር ማስከተሉ ተገለጸ
    መኢአድ በሰሜን ጐንደርና በትግራይ ተጨማሪ ጽ/ቤቶችን ከፈተ
    የመኢአድ የደጀን ወረዳ ልዩ ዞን የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት አካሄድ
    የፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ ዕረፍት አሥረኛ ዓመት ግንቦት 6 ይታሰባል
    Call for a Meeting - ወሳኝ ሰዓት
    መኢአድ በክልል ለሚገኙ የዞን የሥራ ኃላፊዎች ስምምነት በተደረሰበት ሰነድ ላይ ማብራሪያ ሰጠ
    ስለ ምርጫ ስነምግባር ህዝባዊ ስብሰባ በሎንደን ከተማ ተካሄደ