About Us
  • About Kinijit AEUP
  • Political Program
  • Election 2005
  • Election 2010
  • USA
  • Canada
  • Europe
  •   News
  • Amharic
  • English
  • Washington Update
  •   Editorial & Opinions
  • Editorial
  • Opinion
  •   Media
  • Audio
  • Video
  •   Press Release
  • English
  • Amharic
  •   Burning Issues
  • Economy
  • Education
  • Health
  • HR2003 to S3457
  • Regional Crisis
  • Politics & Democracy
  • Others
  •   Facts about Ethiopia
  • All Ethiopia Gallery
  •   Take Action
  • Make a Contribution
  • Join our Supporters
  •    Subscribe to Andenet
         Gazette
      Calendar
  • Calendar
  •  
     
      Home Contact Us   Font help

    የመኢአድ የአርባ ምንጭ ዞን ሰብሳቢና ፀሐፊ ያለ ሕግ አግባብ ታሰሩ


     

    የመኢአድ የአርባ ምንጭ ዞን ሰብሳቢና ፀሐፊ ያለ ሕግ አግባብ ታሰሩ


        
    በጋሞ ጐፋ የአርባ ምንጭ ዞን የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት /መኢአድ/ ሰብሳቢ አቶ ገዛኸኝ ገለቱ እና ፀሐፊው አቶ ሙሉጌታ ወንድሙ መጋቢት 1 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በአርባ ምንጭ ከተማ በሲቀላ ክፍለ ከተማ ፓሊስ ጣቢያ የታሰሩ መሆናቸውን ተገለፀ፡፡
     
    የዞኑ የመኢአድ ሰብሳቢና ፀሐፊ በገዥው ፓርቲ ባለሥልጣናት ለመታስር ያበቃቸው ምክንያት ምልክት ያለበትን ሰንደቅ ዓላማ አልሰቀላችሁም በሚል ሰበብ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡  የገዥው ፓርቲ ሰዎች ሶስት ቀለማት ብቻ ያለበትን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ አውርደው የት እንዳደረሱትም ያልታወቀ መሆኑን ከቦታው የደሰረሰን መረጃ ያስረዳል፡፡
     
    ከዚህ በፊትም በጐፋ ልዩ ዞን ጐፋ ወረዳ መኢአድ ጽ/ቤት ይውለበለብ  የነበረውን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለማት ያሉትን ነባር የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ  ምልክት የለበትም በማለት የወረዳው ፖሊሶች አውርደው መውሰዳቸው ይታወቃል፡፡
     
    መኢአድ በመካኩሉ ኮኮብ የሌለበትን የኢትዮጵያ ባንዲራ ላለፉት አምስት አመታት ሲጠቀምበት የሚታወቅ ሲሆን የካቲት 20 2001 ዓ.ም. በተላለፈው የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ በዞኑ በመኢአድ ላይ በመንግሥት የጸጥታ አባላት የሚፈጽሙትን ሕገ ወጥ ጫና አስመልክቶ አቶ ገዛኸኝ ገለቱ ቃለ መጠይቅ መስጠታቸው ለመታሠራቸው እውነተኛው ምክንያት እንደሆነ አስተያየት ሰጭዎች ይገልጻሉ።
     
    ግለሰቦቹ የታሰሩት ያለ ፍርድ ቤት ማዝዣ ሲሆን በታሠሩ በሦሥተኛው ቀን በዋስ መለቀቃቸውን ከቦታው የደረሰን መረጃ ይጠቁማል።

    Comments



       Type in your comments for this article
    Name (appears on your post)
    Email
    Comment

    Write the characters in the image above

    Search News:
    In all newsIn News Amharic

    Advanced Search
    Archive:
    Published in:
    Published between
    and
    Categories:
    all categories
    one or more of the following categories (select as many as you want)
    History
    World News
    Opinion
    Editorial
    News English
    Washington Update
    News Amharic
    Media Audio
    Media Video
    Kinijit AEUP Radio
    Africa News


    Most Viewed News Amharic
    በምስራቅ ጐጃም አንድ ተማሪ በታጣቂዎች ተገደለ
    በሰሜን ሸዋ ዞን ገዥውን ፓርቲ በመቃወማቸው ለስደት መዳረጋቸውን ገለፁ
    68ኛው የድልና የነጻነት በዓል ተከበረ
    መኢአድ በባሕርዳር ከተማ ታለቅ ስብሰባ አካሄደ - የመጀመሪያዉን የምርጫ ደወል አሰማ
    በሰሜን ጐንደር የእስረኞች አያያዝ አሳሳቢ መሆኑ ተገለፀ
    መኢአድ “ሊበራል ኦፕን-ኤየር ኮሌጅ” መክፈቱን አስታወቀ
    መንግስት ጐንደር ውስጥ ከ6ዐ በላይ ሰዎችን ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ ለአርባ ቀን ያሕል አስሮ መልቀቁ ተገለፀ፡፡
    የጐፋ ልዩ ዞን የገዢው ፓርቲ የጽ/ቤቶቹን ባንዲራ እያወረደበት መሆኑን መኢአድ ገለፀ
    የመኢአድ የደጀን ወረዳ ልዩ ዞን የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት አካሄድ
    የመኢአድ የአርባ ምንጭ ዞን ሰብሳቢና ፀሐፊ ያለ ሕግ አግባብ ታሰሩ